አሚጎስ    (Amigos )

አሚጎስ የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር  የተቋቋመው በኢትዮጵያ የህ/ስ/ማ አዋጅ መሰረት በቁጥር.147/1998 ሲሆን ህጋዊ ስብዕናው ከአራዳ ክ/ከተማ የህ/ስ/ማ ማደራጃ ቢሮ እና ከንግድ ሚኒስቴር በጥር 2005 ዓ.ም ፍቃድ አግኝቶ በስራ ላይ ይገኛል፡፡ አሚጎስ በቀዳሚነት የሚያንቀሳቅሰው የአባላቶች መደበኛ ቁጠባ እና አክሲዮን በመሰብሰብ የተሻለ የብድር አገልግሎት በማቅረብ የተሳለጠ የማህበራዊ ግንኝነቶች እና ኢኮኖሚያዊ ለወጦች በአባላትና በማህበሩ እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡

 

በአሁኑ ሰአት አሚጎስ ከ1700 በላይ አባላቶች ሲኖሩት ከ 70 ሚሊዮን በላይ ሀብት አለው፡፡ በብድር መጠን ከ 100 ሚሊዮን ብር በላይ  ለ 700 አባላት እስከ አሁን ያቀረበ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ብር 60 ሚልዮን ከ 300 በላይ አባል ተበዳሪዎች በስራ ላይ ይገኛል፡፡ ወደ አንድ ሚሊዮን ብር ደግሞ በ 6 የተመረጡ ባንኮች አክሲዮን ተገዝቶ ተጨማሪ የአባልት  ጥቅም ከፍ ያደርጋል፡፡

ራእይ

 

በአባላቶቹ ቁጥር አንድ ተመራጭ የሆነ የገንዘብ አገልግሎት ሰጪ ማህበር መፍጠር ነው፡፡

 Vision

To be the most preferred financial services provider to its members

ተልእኮቻን

ጥራት ያለው የገንዘብና ኢ-ገንዘብ አገልግሎት በማቅረብ የአባላት ኢኮሚያዊና ማህበራዊ ስራዎች በመስራት የአባላትን ኑሮ ወደ ተሻለ ደረጃ ማሳደግ ነው፡፡