About Us

አሚጎስ የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር  የተቋቋመው በኢትዮጵያ የህ/ስ/ማ አዋጅ መሰረት በቁጥር.147/1998 ሲሆን ህጋዊ ስብዕናው ከአራዳ ክ/ከተማ የህ/ስ/ማ ማደራጃ ቢሮ እና ከንግድ ሚኒስቴር በጥር 2005 ዓ.ም ፍቃድ አግኝቶ በስራ ላይ ይገኛል፡፡ አሚጎስ በቀዳሚነት የሚያንቀሳቅሰው የአባላቶች መደበኛ ቁጠባ እና አክሲዮን በመሰብሰብ የተሻለ የብድር አገልግሎት በማቅረብ የተሳለጠ የማህበራዊ ግንኝነቶች እና ኢኮኖሚያዊ ለወጦች በአባላትና በማህበሩ እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡

በአሁኑ ሰአት አሚጎስ ከ 1700 በላይ አባላቶች ሲኖሩት ከ 60 ሚሊዮን በላይ ሀብት አለው፡፡ በብድር መጠን እስከ 100 ሚሊዮን የሚጠጋ ለ 500 አባላት እስከ አሁን ያቀረበ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ብር 50 ሚልዮን ከ 300 በላይ አባል ተበዳሪዎች በስራ ላይ ይገኛል፡፡ ወደ 1ሚሊዮን ብር ደግሞ በ 6  የተመረጡ ባንኮች አክሲዮን ተገዝቶ ተጨማሪ የአባልት  ጥቅም ከፍ ያደርጋል፡፡

Organizational profile

Background

Amigos Saving and Credit Cooperative Association (Amigos SACCO) is a financial cooperative established by a team of young and professional friends. The legalization process has been finalized and come into existence by obtaining a license from Arada Sub-City Cooperative Promotion Office and registered with the ministry of trade in January 2013. On the date, Amigos comprised 20 members with nearly Birr 10,000.00 deposit at the United Bank. Currently, Amigos involves more than 1700 members with over 40.2 million birr mobilized savings and 11.3 million birrs paid-up capital respectively. Currently, Amigos has around 60 million Total Assets and 60 million Total liabilities.

 1. ራእይ

በአባላቶቹ ቁጥር አንድ ተመራጭ የሆነ የገንዘብ አገልግሎት ሰጪ ማህበር መፍጠር ነው፡፡

   Vision

To be the most preferred financial services provider to its members

   2. ተልእኮቻን

ጥራት ያለው የገንዘብና ኢ-ገንዘብ አገልግሎት በማቅረብ የአባላት ኢኮሚያዊና ማህበራዊ ስራዎች በመስራት የአባላትን ኑሮ ወደ ተሻለ ደረጃ ማሳደግ ነው፡፡

Mission

In developing its mission statement, Amigos considered the economic, financial and technological trends in the society system nationally and regionally and the financial industry as whole. The society identified its internal strengths and challenges and external opportunities and challenges. Finally, the SACCO identified those areas that it could reasonably influence.

3. ዓላማችን

የአባላትን አቅም መሰረት ያደርገ መደበኛ ተቀማጭ በመሰብሰብ ለአባላቶች ተደራሽ፣ አዋጪ፣ ምቹ እና ቀልጣፋ የፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት አባላቶችን  የተሻለ መተዳደሪያ እንዲኖራቸው ማገዝ ሲሆን የሚከተሉትን ያካትታል

 •  አባላት በተናጠል በመስራት ሊወጥዋቸው ያልቻሉት ችግሮች በጋራ መፍታት
 • አባላት ያላቸውን ዕውቀት፣ሀብትና ጉልበት በማቀናጀት
 •  አባላቶች አትራፊ በሆኑ የንግድ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ እንዲሁም የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያገኙ መርዳት
 •  ለአባላት የብድር የሕይወትና ማህበራዊ መድን ዋስትና መስጠት፤
 •  በአባላቱም ሆነ በአካባቢ የሚገኝ ህብረተሰብ ማህበራዊ ጉዳይ ዉስጥ ተሳታፊ መሆን

    Objective

The main aim of the institution is to deliver accessible and efficient financial services to members. Besides providing financial services, it is also to be engaged in profitable and meaningful investments to improve the living standard of members.

Specific objectives

 • To enhance the saving and credit culture of members
 • Mobilize regular savings from members to provide better size loans
 • To create an operational and financially sustainable institution
 • To generate significant profit; make annual dividend to shareholders/members
 • To participate in profitable and feasible investments/business

4. ተግባር

 • ለአባላት ገንዘብ ማበደርና ከነወለዱ መሰብሰብ
 • አባላት ተበድረው አዋጭ በሆነ የስራ ዘርፍ እንዲሰማሩ የምክርና ስልጠና አገልግሎት መስጠት
 •  ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን ማፍራትና ማስተዳደር
 • የአካባቢ ልማት ላይ መሳተፍ፤
 • ስለ አባላትና ማህበሩ እድገት ጥናት እና ምርምር ማካሄድ፤
 • ሌሎች አግባብነት ያላቸዉን ተመሳሳይ ተግባራት ማከናወን

5. እሴቶች

አሚጎስ የሚከተሉትን እሴቶች አሉት፡-

ብቃት ያለው አመራር ፣ ለጋራ አላማ በህብረት መስራት፣ አርቆ ለውጤት ማቀድ፣ ተጠያቂነት ፣ መተሳሰብ ፣ ታማኝነት እና አንድነት ናቸው፡፡

አሚጎስ እንዴት አባል መሆን ይቻላል

አሚጎስ አባል ለመሆን ከታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት ያስፈልጋል፡

Q እድሜ 18 አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ

Q  የመመዝገቢያ ፎርም መሙላት

Q መነሻው ትንሹ የአክሲዮን መጠን ግዢ መክፈል

Q  ወርሃዊ የቁጠባ መጠን መነሻ 500 ብር

Q ለልጆች ቁጠባ የመመዝገብያ ክፍያ ሳይኖረው መነሻ ብር 50  መክፈል

Q  ሁለት የፓስፖርት መጠን ያለው ፎቶግራፍ

Q  የመታውቂያ ኮፒ

Q የቁጠባ ቀናት ከ 28 እስከ 03  በኢትዮጵያ አቆጣጠር በየወሩ መክፈል